ደስታን አብሳሪ ምስራች ነጋሪ
ቅዱስ ገብርኤል ሆይ ናልን ከሰማይ
1.ለማርያም በናዝሬት እንዳበሰርካት
ተቀብለህ ስጠን የሰላም መልዕክት
በጦርነት በረሀብ ተቃጥለናልና
የምስራቹን ቃል ቶሎ ይዘህልን ና
ደስታን አብሳሪ ምስራች ነጋሪ
ቅዱስ ገብርኤል ሆይ ናልን ከሰማይ
2.በጣሞ ስንደክም ከኋላ ስንቀር
አማልደን ከጌታ ወድቀን እንዳንቀር
ቃልህ የሚጣፍጥ ሳለ እንደማር
አሁንም አሁንም ደጋግመህ አብስር
ደስታን አብሳሪ ምስራች ነጋሪ
ቅዱስ ገብርኤል ሆይ ናልን ከሰማይ
3.የደስታን ዜና ይዘህ የምትመጣ
በዓለማችን ላይ ሰላም እንዲመጣ
የምስራች ንገር ለአሕዛብ በሙሉ
የአምላክ ልጆች ናቸው አንድም ሳይቀር ሁሉ
ደስታን አብሳሪ ምስራች ነጋሪ
ቅዱስ ገብርኤል ሆይ ናልን ከሰማይ
