ሥምህን ጠርቶ

-

ሥምህን ጠርቶ ማን አፍሮአል ጌታ
አንተን ይዞ ወጥቶ ማንስተሪታ
ክንደ ብርቱ ነህ ጌታ አምላካችን

ስትሰራ አይተናል ጌታ እኛም በዓይናችን
ስትፈውስ አይተናል የሱስ በዘመናችን

1. ስምህን ይዞ ዳዊት ሲወጣ
ይድን ነበረ ከብዙ ጣጣ
ባንተ እርዳታ ጐልያድም ወድቋ
ባሪያህም በእምነት ድልን አግኝቷል

2. የመቶ አለቃው ልጅ አጅግ ታሞ
ሊሞት ሲያጣጥር በጣም ተዳክሞ
ባትገባም ቤቱ ከጣራው በታች
ልጁን ፈወስከው ሆነ መስራች

3. እንደምትፈውስ ዝናህን ሰምተው
አስር ለምጻሞች ወዳንተ መጥተው
ሲማፀኑህም እንድትረዳቸው
ፈጥነህ ከለምጻ አነፃሃቸው

4. ዙሪያችንን ችግር ስክበን
የሚያፅናና አይዞህ ባይ አጥተን
ስምህን ስንጠራህ የሰማህ ጌታ
ምንም ሳትዘገይ መጣህ በአንድ አፍታ

የምስጋና

Leave a Comment

Scroll to Top