ደግሞ ካበቃኸኝማ

-

አዝ. ደግሞ ካበቃኸኝማ አንተን ለማመስገን
አንተን ለማመስገን
እኔ አመልክሀለው ሳልሰለች ሌት ከቀን
ወደህ ከመረጥከኝማ አንተን ለማመስገን
አንተን ለማመስገን
እኔ አመልክሀለው ሳልሰለች ሌት ከቀን

1. እግሬ ይበል እንጂ ጠፋ ወጣ ወጣ
ጠፋ ወጣ ወጣ
ልቤማ መች ያርፋል አምላኬ አንተን ሲያጣ
የሱሴ አንተን ሲያጣ
ደግሞ ካበቃኸኝ ፀጋ ውስጤ ሞልቶ
ዜማ ባፌ ሞልቶ
እኔ ካንተ አልቀረም አረሳህም ከቶ
ምንህ ተሰልችቶ

ያላንተማ/2/ የሱሴ   አልችልም/አልኖርም/     እኔማ/2/
ያላንተ አልኖርም ያላንተ አልችልም መዋልም ማደርም
ያላንተ አልችልም ያላንቸ እኔ አልችልም እስትንፋስ የለኝም

2. ባገር በመንደሩ ምትወደው ባልጠፋ
ሚወደድ ባልጠፋ
እኔን ካበቃኸኝ ዘምር ካልከኝማ
ከቀባኸኝማ
እጣዬ ወደቀ በመልካም መንገድ ላይ
ባማረ መንገድ ላይ
ሌላ ጥማት የለኝ እኔ ከዚህ በላይ
እኔ ካንተ በላይ

ያላንተማ/2/ የሱሴ   አልችልም/አልኖርም/     እኔማ/2/
ያላንተ አልኖርም ያላንተ አልችልም መዋልም ደርም
ያላንተ አልችልም ያላንቸ እኔ አልችልም እስትንፋስ የለኝም

አዝ. ደግሞ ካበቃኸኝማ አንተን ለማመስገን
አንተን ለማመስገን
እኔ አመልክሀለው ሳልሰለች ሌት ከቀን
ወደህ ከመረጥከኝማ አንተን ለማመስገን
አንተን ለማመስገን
እኔ አመልክሀለው ሳልሰለች ሌት ከቀን

የምስጋና
Amharic
St.Gabriel

Leave a Comment

Scroll to Top