ቀና ብዬ አንተን ልጠራህ ስሞክር
ይቅርብህ ይለኛል ወደኋላ እንድቀር
ደግሞ እተወውና ጌታ ጌታ እላለሁ
ትንሽ እቆይና መልሼ እወድቃለሁ
ጌታ እባክህ ናልኝ አውጣኝ ከፈተና
በአለም ተከብቤ ወድቅያለሁና/2/
ለመምጣት ስዘጋጅ ምልክት አይና
አለም ያስረሳኛል ያባብለኝና
ዙሪያዬ በሙሉ ክርስቲያን የለበት
አሳሳች ብቻ ነው እሾሁ የበዛበት
ጌታ እባክህ ….
ሩጫ ስድብ ስረቆት ሐሰትንም ክጄ
ልከተልህ መጣሁ ህይወትን አፅንቼ
በንስሐ በፆም በፀሎት ታግዤ
ነው ያሸነፍኳቸው ባንተ ሃይል ተይዜ
ድኛለሁ በስምህ በሃይል አምላኬ
ተመስገን ልበልህ ምን አለኝ ጌታዬ/2/
ስለዚህ ያንተ ነኝ ሌላ አምላክ የለኝም
ተመስገን ልበልህ ዛሬም ለዘላለም
አልፋና ኦሜጋ ክበር አምላካችን
ከማጥ ያወጣኸን እኛን ልጆችህን
ድኛለሁ በስምህ….
