ዚኪሞ

-

1. መጀመሪያውና መጨረሻው የሆነው
አልፋና ኦሜጋ በዙፋኑ ያለው
ትላንት ለተጠማ ውኃ ምንጭ የሆነው
ጨለማን በብርሃን አዲስ ቀን ያደረገው

አዲስ ሰማይንና አዲስ ምድርንም አየን
የእግዚአብሔር ድንኳኖች በምስጋና ሞልተን
አዲሲቷ ከተማ ደሞቀ አንደሙሽራ
በአዲስ ዘመን ይመስገን ስለአርሱ ብቻ ይወራ

ተመስገን ጌታ ተመስገን ዛሬ ተመስገን
ተመስገን ጎይታና ተመስገን ሎሚ ተመስገን

2.እያንዳንዷን ቀን ባርኮ ሆኖ መሃላችን
ፍቅርን አውርዶ በመሃከላችን
ስለ እግዚአብሔር እናውራ ስለ እግዚአብሔር ይነገር
ምን እንለዋለን ከተመስገን በቀር

የማይነቃነቅ መሰረቱ ጠንካራ
ትናንትና ዛሬ ነገም የሚያኮራ
ዘመን ዘመናትን በርሱ ብርታት አልፈን
ከእግዚአብሔር ጋር ኖረናል ከእርሱ ጋር እንኖራለን

ኑቶሊ ያዋቃ ኑቶሊ ሃራ ኑቶሊ
ሽኩራኸ ጉዌታ ሽኩራኸ ዐኩዋ ሽኩራኸ

3.አንዴት ያስደንቃል የሆነልን ነገር
ሳንሰጋ ሳንፈራ ሆነን በእግዚአብሔር
በርሱ ጥበቃ ስር ኮርተን ተደላድለን
ዘመን ዘመናትን አያሸጋገረን

ዛሬ በደስታችን ቀን በአዲሱ ዘመን
ለእግዚአብሔር ምስጋና ሰንቀን ከልባችን
ካለንበት ታድመን ቤቱን በፍቅር ሞልተን
ዛሬም ነገም እያልን ከልባችን ተመስገን

ገለታ ጦሳው ገለታ ሀቺ ገለታ
ዚኪሞ ዚኪሞ ሌሎ ሌሎ ዚኪሞ

ኢል ሲኞራ ሲያ ሎዳቶ ሲያ ሎዳቶ
መርሲ ዲያ መርሲ መርሲ ዲያ ኦዥሪድ ሜርሲ

የምስጋና

Leave a Comment

Scroll to Top