1.ማነው እንደ ማርያም ባለውለታ
ለፈጣሪ ታዛዥ ሳታመነታ
አዲሲቷ ሔዋን ሕይወት ሰጠችን
እኛንና እግዚአብሔር አገናኘችን አስታረቀችን /2/
ክብር ለኢየሱስ እናት ክብር
ክብር ለንጉሡ እናት ክብር
ክብር ለአማላጃችን ክብር
ክብር ለድንግል ማርያም ክብር
2. ልጇ ለዓለም ሁሉ መድኃኒት ነው
ፍቅሩ የማይለወጥ ለዘላለም ነው
ምሕረት ቸርነቱ እጥፍ ድርብ ነው
ሁሉንም የያዘው ኢየሱስ ጌታ ነው/2/
ክብር ለኢየሱስ እናት ክብር
ክብር ለንጉሡ እናት ክብር
ክብር ለአማላጃችን ክብር
ክብር ለድንግል ማርያም ክብር /2/
