አዝ. ቅድመ ዓለም ታስባ ስትኖር የነበረ
የጌታን መወለድ ለእርሷ የተበሰረ
ከፍጡራን በላይ ከፈጣሪ በታች
ተስፋችን የሆነች ድንግል ማርያም ነች
1. ደስታና ፍስሀ ለፍጥረት ያደለ
እኛን ከባርነት ሊያድን የታገለ
እናቱ ብትሄድ ወደ ኤልሳቤጥ
ጽንሱ እንኳን ዘለለ በመገላበጥ
አዝ. ቅድመ ዓለም ታስባ ስትኖር የነበረ
የጌታን መወለድ ለእርሷ የተበሰረ
ከፍጡራን በላይ ከፈጣሪ በታች
ተስፋችን የሆነች ድንግል ማርያም ነች
2. ንጉሡ ውበቷን ስለወደደላት
በረቂቅ ጥበቡ ፍጹም ተዋሀዳት
መለኮት አደረ በእርሷ ማኅፀን
በድንግል ማርያም ብርሃን ወጣልን
አዝ. ቅድመ ዓለም ታስባ ስትኖር የነበረ
የጌታን መወለድ ለእርሷ የተበሰረ
ከፍጡራን በላይ ከፈጣሪ በታች
ተስፋችን የሆነች ድንግል ማርያም ነች
3. እራሱ መስርቶ እራሱ አጽንቷት
አምላክ እርሷን ወዶ በፍጹም መርጧት
በመሆን ብትገኝ የእግዚአብሔር ብርቅ! እቃ
ከእርሷ ተዋህዶ ግዞትም አበቃ
አዝ. ቅድመ ዓለም ታስባ ስትኖር የነበረ
የጌታን መወለድ ለእርሷ የተበሰረ
ከፍጡራን በላይ ከፈጣሪ በታች
ተስፋችን የሆነች ድንግል ማርያም ነች
4. ከማርያም ተወልዶ ጌታ ቢሞትለት
አዳምም አገኘ ያጣውን ልጅነት
ተመልሶ ገባ ወደ ቀድሞ አገሩ
ድንግልን አድርጎ ዋልታና ማገሩ
አዝ. ቅድመ ዓለም ታስባ ስትኖር የነበረ
የጌታን መወለድ ለእርሷ የተበሰረ
ከፍጡራን በላይ ከፈጣሪ በታች
ተስፋችን የሆነች ድንግል ማርያም ነች
