ምስጋናዬ ሙሉ ነው

-

ምስጋናዬ ሙሉ ነው /4/

ላንተ ያለኝ እጅግ ብዙ ነው
እግዚአብሄር እጅግ ታላቅ ነው
ማደሪያህን ይሙላው ተቀበለው /2/

1. ሰምተኸኛል ልመናዬን
አድምጠኸኛል ጌታ ጸሎቴን
አላሳፈርከኝም ጌታ
ይልቁንም በምስጋና ሞላኸኝ ተመስገን አባ /2/

ምስጋናዬ ሙሉ ነው /4/

ላንተ ያለኝ እጅግ ብዙ ነው
እግዚአብሄር እጅግ ታላቅ ነው
ማደሪያህን ይሙላው ተቀበለው /2/

2. ሰማህለት ልመናውን
አዳመጥክለት ጌታ ጸሎቱን
አላሳፈርከውም ጌታ
ይልቁንም በምስጋና ሞላኸው ተመስገን አባ

3.ሰማህላት ልመናዋን
አዳመጥክላት ጌታ ጸሎቷን
አላሳፈርካትም ጌታ
ይልቁንም በምስጋና ሞላሃት ተመስገን አባ

የበዛው ምስጋና ልሰዋልህ ጌታ
ተመስገን ተመስገን ጌታ
የበዛ ምስጋና ልሰዋልህ ጌታ
ተመስገን ተመስገን ጌታ /2/

ተመስገን /4/
ተወደስ /4/

የምስጋና

Leave a Comment

Scroll to Top