እንደ እስራኤል ህዝብ በድል መራኸን
ከስንቱ ጥፋት እየጠበከን
አልደከመንም ሆነን ካንተ ጋር
በቤትህ አለን በድል አምረናል /2/
አዝ. አምረናል /4/ ደምቀናል /4/
1. ባንተ ቸርነት ባንተ እርዳታ
እዚህ ደርሰናል ተመስገን ጌታ
ነገን በተስፋ እናየዋለን
ሁሉን ቻይ ጌታ ባንተ ተማምነን
አንተን ታምነን እንበረታለን
ካንተ ጋራ እንሻገራለን /2/
አዝ. አምረናል /4/ ደምቀናል /4/
2. ጌታ ባትረዳን ባትሆን ከኛ ጋር
ያለፍነው ሁሉ እንዴት ይቻላል
አቅም ሰጠኸን ሆንከን ብርታት
ዛሬን አየነው ባንተ ተማምነን
ክንድህ ክንድህ እየደገፈን
ስንቱን አለፍን እየጠበቀን /2/
አዝ. አምረናል /4/ ደምቀናል /4/
3. በፀጋህ እንጂ ባንተ ምህረት
በአንተ ፍቅር በደግነትህ
ህይወታችንን አደላደልከው
ምን እንላልን ክበር ብቻ ነው
ክበር ክበር እንልሃለን
አንተን ብቻ እናመልካለን /2/
አዝ. አምረናል /4/ ደምቀናል /4/
