እረኛዬ መሠማሪያዬ /2/
የአይኔ ማረፊያ የመንገዴ ብርሃን /2/
እረኛዬ መታመኛዬ
1. ጠላቴ ልክ እንደ አንበሳ ዙሪያየን ቢዞር ቢያገሳ
እግዚአብሄር እረኛዬ ነው ሚያስፈራኝ ማነው /2/
ባላንጣዬ ሲበረታ ሲመስለው የማይረታ
እግዚአብሄር እረኛዬ ነው ሚያስፈራኝ ማነው /2/
በጨለማ ብከበብም ክፉውን አልፈራ
እግዚአብሄር አለ ከኔ ጋራ
በሞት ጥላ ብራመድም ክፉውን አልፈራ
እግዚአብሔር አለ ከኔ ጋራ /3/
እግዚአብሔር ሁሌ ከእኔ ጋራ /2/
2. ከሳሾቼ ሲሰለፉ ሲያጠምዱ ነፍሴን ሊያጠፉ
እግዚአብሔር እረኛዬ ነው የሚያስፈራኝ /የሚያሰጋኝ/ ማን ነው /2/
አሳዳጆቼ ሲዝቱ ሲመኙ ሊያረጉኝ ከንቱ
እግዚአብሄር እረኛዬ ነው የሚያስፈራኝ /የሚያስጋኝ/ ማን ነው /2/
በኢዮብ ላይ እንደዋሸው ጠላቴ ቢዋሽም
እግዚአብሄር ግን ፈጽሞ አልጣለኝም /2/
እግዚአብሄር ግን አንዴም አልተወኝም /2/
