ወልደ አምላክ

2

ወልድ አምላክ ተወለደልን
በእቢልታና ባማረ ዜማ

ወልድ አምላክ ተወለደልን
ደስ ይበለን ምክሩን እንስማ

እንዴት መልካም እንዴት ውብ ነው
በእውነት ፊቱ የአምላክ መልክ ነው
እንዴት መልካም እንዴት ውብ ነው
ሰላማችንም እርሱ ነው

እበረት ሆነ ማደሪያው
ጉዝጓዙም ሳር ገለባ ነው
እበረት ሆነ ማደሪያው
ቢያፈቅረን ነው ሰው የሆነው

በእውነት የአምላካችን ልጅ ነው
ገነትን ለኛ ያበጀው
በውነት የአምላካችን ልጅ ነው
ለኛ ስጋ የለበሰው

አማኑኤል ቢወለድልን
አምላካችን ይቅር አለን
አማኑኤል ቢወለድልን
ሌት ሄደ ብርሃን ነጋል

የልደት

Leave a Comment

Scroll to Top