መድሃኒት ኢየሱስ ብቻ ነው

6

መድሐኒት ኢየሱስ ብቻ ነው
ብዙ መልካም ላመነው
ልከተለው ልውደደው
በርሱ እጅ ነው መዳኛው

የኔ ኢየሱስ ቅኑ ጌታ
ለኔ ብሎ ተንገላታ
ሐይል እያለው የበረታ
ተጨነቀ በጐልጐታ

በጭነቅህ እኔ ልጨነቅ
መከራህንም ልወቅ
ከመስቀልህ ኣልራቅ
ከናትህ ጋር ልጠብቅ

እናትህ ቆማ ያየሐት
ልቧን እሳት ሲፈጃት
የሐዘን ሰይፍ ሲወጋት
ይጨንቀኛል ሳስባት

መሐሪ ከልብህ ማረኝ
ከመከራህ አካፍለኝ
ወዳንተ ዘንድ አቅርበኝ
በመንግስትህ አስበኝ

ገመድህ እኔን ይሳበኝ
ግርፋትህ ይግረፈኝ
በችንካርህ ቸንክረኝ
ንፁህ ደምህ ይጠበኝ

በመስቀል የፈሰሰው ደም
ቤዛ ሆነ ለአለም
እኔን ያንሳኝ ከድካም
በአንቺ ልመና ማርያም

የልደት

Leave a Comment

Scroll to Top