ትልቅ ድንቅ ታየ በቤተልሔም ከተማ
ታይቶ የማይታወቅ በጆሮም ያልተሰማ
ጌታችን ወርዶአል ከሰማይ ሰማያት
በግርግም ተኝቷል
እራሱን አዋርዷል ክብርም ይገባዋል
መወለዱ ያሻናል ብዙ ጭንቅ አለብን
እሱ ይፈውሰናል ምንም ቢፀናብን
ስንፈልግ ስንሻ መጥቷል ወደኛ
እኛን ለማዳን ነው በበረት የተኛ
አህዛብ ሁላችን እናቅርብ ምስጋና
ችግራችንን አይቶ መጥቶልናልና
ከነበረን ደዌ ሊያወጣን ጌታችን
እነሆ ይኸውና እንስጠው ልባችን
እነሆ ግልፅ ሆነ የአምላክ ቸርነቱ
በበረት አስተኛው ለኛ መሳሳቱ
ንጉሥ ሆኖ ሳለ ምንም ሳይቸግረው
ለእኛ እንዲዋረድ ፍቅር አስገደደው
