ለአንተ እንስገድ

7

ለአንተ እንስገድ መስቀል ሆይ
ኢየሱስ አለ በአንተ ላይ/2/

ለአንተ እንስገድ መስቀል ሆይ
ጨንቆት አልጋው ጌታችንን
እንሳለም አንተን ቀርበን
በአንተ ሆኖ ተቤዥን

ለአንተ እንስገድ መስቀል ሆይ
ክብር የሌለው እንጨት ነበርክ
ጌታ ክርስቶስ ተሰቅሎብህ
ለኛ ሁሉ መጠጊያ ሆንህ

ለአንተ እንስገድ መስቀል ሆይ
ጌታ አረገህ እጮኛው
ክንዱን በአንተ ዘረጋው
ሰውን ሁሉ ሊያድነው

ለአንተ እንስገድ መስቀል ሆይ
የጌታ ደም ቀደሰህ
እንባው ደግሞ አራሰህ
ሰውን ከአምላክ አስታረቅህ

ለአንተ እንስገድ መስቀል ሆይ
የጐልጐታ ስቃይህን
እንዳይረሳው ልባችን
ስበርልን ብርታቱን

ለአንተ አንስገድ መስቀል ሆይ
ሞተን ከአለም ስንለይ
በፍርድ ቀን እዚያ ላይ
አንተ አብራልን እንደፀሐይ

የልደት

Leave a Comment

Scroll to Top