ልብሽ በሐዘን እንደሚባባ
ለልባችን ሁኚ ባልደረባ
ማርያም ሆይ የለቅሶሽ እንባ
አንዲረዳን እኛ ልብ ይግባ
ስለኛ ብሎ ልጅሽ ተሰቅሎ
ልብሽ በሀዘን ተወግቶ ቆስሎ
ስለኛ ብሎ ልጅሽ ተሰቅሎ
እንዳንጠፋ ነይ እርጅን ቶሎ/2/
እነሆ እናት ሰጥቶናል
እንዳንተው ልጅነትን
የልብሽ ሰይፍ ይጠብቀን
የአለም ክፋት እንዳይዘን
እሸክም ከአንቺ ሐዘን
የአቅማችንን ተካፍለን
አንቺ አልቅሰሽ እናታችን
እኛ በአለም ደስ አይበለን
ከመስቀል ኣውርደውት
ተደግፎ በአንቺ ደረት
ያለቀሽው የእንባ ሙላት
ይጠብቀን እኛን ከክፋት
