ፍቅርህ ደነቀኝ ፍቅርህ ደነቀኝ
ቀመስኩት ጠጣሁት እጅግ ጣፈጠኝ
ከወይን ጠጅ ይልቅ ደስ አሰኘኝ
ልገልፀው አልችልም ቃላት አጠረኝ
ለፃድቅ ሰው ሲል አሳልፎ የሚሞት
በጭንቅ በስቃይ ይገኛል ድንገት
ለእኔ ሐጥያተኛው ውዴ ሲሞት
እንዴት ወደደኝ ምን አስደስቶት
እንዳልወድቅበት እጄን ይይዛል
ኮብልዬ ስሄድ ደግሞ እጅግ ያዝናል
ሐጥያት በደሌ ቢያስቸግረውም
ፍቅር ነውና ቂም አያውቅም
ውዴ በእኔ ላይ አላማው ፍቅር ነው
የእርሱን ምኞት ወደእኔ ነው
በቸርነቱ የተነሳ ነው ያልጠፋሁት
እንደኔ ቢሆን ሞቼ ነበር ጥንት
በዘለዓለም ፍቅር እኔን ወደደኝ
በእጆቹ መዳፍ ውስጥ ቀረፀኝ
በህይወት መዝገብ ላይ እኔን አኖረኝ
ዳግም ይመጣል ውዴ ሊወስደኝ
