አየሁ ፍቅር

13

አየሁ ፍቅር በመስቀል
የማይደበዝዝ የማይቀየር
ከፀባኦት የወረደ
ሁላችንን የወደደ

ከጎልጎታ የሚታይ
ታላቅ ታናሽን የማይለይ
ከእግዚአብሔር ዘንድ የተላከው
ኦ ፍፁም ፍቅር ኢየሱስ ነው

ሁላችንን የወደደ
ከአባቱ ክብር የወረደ
ከእግዚአብሔር የተሰጠ
ታላቅ ፍቅር ተገለጠ

ክብሩን በውርደት ለውጦ
እስራታችንን ከእኛ ቆርጦ
የእኛን እዳ ሊከፍል
ፍቅር ታየ በመስቀል

በቀራኒዮ የታወጀው
ከፍ ብሎ የታየው
ከፀባኦት የተላከው
እፁብ ፍቅር ኢየሱስ ነው

የልደት

Leave a Comment

Scroll to Top