አምላኬ ሆይ ሞት ስትፈርድብኝ
የመምጫውን ቀኑን ደብቀኸኝ
በደግነት እንድኖር አደረከኝ
የእውነት ፍርድህ እዳያስፈራራኝ
ገሩ ኢየሱስ
የምታልፋት በዚህ አግድም
ሐብታሞችም ደግሞ ድሆችም
ከመቃብር እዩት የእኔ አዕም
ስለእናንተም ይህ አይቀርም
ዋ ሰው ሆይ
በዚህ ድንጋይ የፃፈውን
ቅረብና አንብበው ስሜን
ክፈትና ተመልከተው ውሰጤን
እሬሳዬ የመሰለውን
ዋ ሰው ሆይ
በውበቴ በአፍላ ልጅነቴ
ብዬ ነበር ብርቱ ነው ህይወቴ
ድንገት ሆነ መውደቄና መሞቴ
አለሁ አትበል አንተም በህይወቴ
ዋ ሰው ሆይ
ስጋ ተላላ አፈር ሆነ ትሉ
የኛ ስጋ አፈር ነው በሙሉ
አፅሞች እንኳን ልይት ልይት ይላሉ
ለአዳም ያለው እግዜር ይህ ነው ቃሉ
ዋ ሰው ሆይ
እኔን አይተህ ለራስህ አስብ
የማይቀር ነው ሞት ለሰው አደብ
ተከታይ ነህ በጣም አርገው ልብ
ተሰናድተህ ጠብቅ በጥበብ
ዋ ሰው ሆይ
