በመሞቴ ሞቶ በመቁሰሌ ቆስሎ
መዋረድ መርጦ በሰዎች ፊት ቆሞ
እዳዬን ቻለልኝ ያታላቅ ፈጣሪ
ነፍሴ ደስ ይበልሽ በአምላክሽ ኩሪ
አምላኬ እንደሞተ አውቃለሁ
የህይወት ውሃ ከእርሱ ጠጥቻለሁ
አምላኬ እንደሞተ አውቃለሁ
የዘለአለም ህይወት በእርሱ አግኝቻለሁ
ጌታ ባይሞትልኝ ባይዋረድ ኖሮ
ህይወትን ሳያዩ ዘለአለም ተቀብሮ
መኖር ብቻ ነበር ያለኝ አማራጭ
ጌታዬን አገኘሁ ሙሉ ህይወት ሰጭ
አንተስ ወንድሜ ሆይ አገኘህ ሆይ ጌታን
በመስቀል ተሰቅሎ ከሞት የተነሳውን
ካላየህ ና እየው ህይወት ይሰጥሃል
እዳህን በመስቀል ለአንተም ከፍሎልሃል
ኣንቺም እህቴ ሆይ አገኘሽ ሆይ ጌታን
በመስቀል ተሰቅሎ ሞቶ የተነሳውን
ካላየሽ ነይ እይው ህይወት ይሰጥሻል
እዳሽን በመስቀል ለአንቺም ከፍሎልሻል
