1. ሞትና መውጊያው አያገኘንም
የጠላት ዛቻ አያስፈራንም
የሲኦልን በር በሞትህ ዘግተሃል
ለኛ ለሕዝብህ ሕይወት ሆነሃል
ከክብር በላይ ክብር ከሞገስም በላይ ሞገስ
ከዝናም በላይ ዝና ታላቅ ስም ያለህ ገናና
እናከብርሀለን ልጆችህ ድነናልና በሞትህ
ዋጅተኸናልና በደምህ እንዘምራለን ለክብርህ
2. ጠላት ሊከበን ዙሪያችን ቢዞር
ካንተ ሊለየን ሊነጥላን ቢያሴር
ይደክማ እንጂ አያገኘንም
ከአንተ እቅፍ ሊያወጣን አይችልም
3. ደመናም ባይኖር ነፋስም ባይነፍስ
ሳትረካ አታድርም የተጠማች ነፍስ
ምናመልክህ አምላክ እጅህ ሙሉ ነው
ታዲያ የሚያስፈራን የሚያውከን ማነው
