ተነሳላችሁ

18

ተነሳላችሁ ደስ ይበላችሁ
ከእግዜርም ጋር አስታረቃችሁ
ሰብሮ መቃብሩን ተነሳልን
የአለም ንጉስ ተነሳ ኢየሱስ
ሃሌሉያ/3/

ሽቶዋን ይዛ ለመቃብሩ
ገና ሳይመጡ ደቀመዝሙሩ
ደረሰች በፊት መቅደላዊት
ብትመለከት ማንም የለበት
ሃሌሉያ/3/

ጧዋት በማለዳ ገና ሳይነጋ
ጴጥሮስ ዮሐንስ ተነሱ አንድጋ
ሊያይ ገባ ጴጥሮስ ወደ መቃብር
ትንሣኤን አመነ ሳይጠራጠር
ሃሌሉያ/3/

መቃብሩንም ሲያይ በጣም
ታያቸው መልአክ ለብሶ ብርሃንም
ጌታ ተነስቷል እዚህ የለም
ገሊላ ሄድዋል ተናግሯል ቀድሞም
ሃሌሉያ/3/

ደቀ መዛሙርቱ ማታ በውድቀት
ተሰብስበው ሳሉ ሁሉ ባንድነት
ጌታ መጣላቸው እመሃላቸው
እንዴት ደስ ይላቸው ሰላም ሲላቸው
ሃሌሉያ/3/

ቶማስ ቢጠራጠር በትንሣኤው

ኢየሱስ ተገለጠ ሊያሳምነው
አትጠራጠር ቁስሌን እየው
እኔ ነኝ እመን ጥርጣሬን ተው
ሃሌሉያ/3/

እስይ ተነሳልን ደስ ይበለን
ስብሐት ለማርያም ልጅ ድል ለነሣልን
ይክበር ይመሰገን ለዘለዓለም
በእውነት እርሱ ነው መድኃኔ ዓለም
ሃሌሉያ/3/

ዲዲሞስ አመነ ስላየ ቁስሉን
የችንካሩን ቦታ የእግሩንና የእጁን
ወድቆም እመሬት ሰገደለት
አምላኬ ጌታዬ አንተ ነህ በእውነት

የትንሳኤ

Leave a Comment

Scroll to Top