ኢየሱስ

22

አለምን ለማዳን መወለድን
በድህነት መኖርን
በመሳም ተላልፎ መሰጠትን
እንደወጀለኛ መታሰርን /2/
እንደ ንፁህ በግ ለመስዋት መጎተትን
በምድራዊ ፈራጆች ፊት አላግባብ
መቆምን /2/

ነፍሱን ለኔ የሰጠው ለራሱ ሳይራራ
ይክበር ይንገስልን አሜን ሀሌሉያ /2/
ይህን ለእኔ የተሸከመው ኢየሱስ
ይህን ሁሉ የታገሰው ኢየሱስ
ይህን ለእኔ የተሸከመው ኢየሱስ
ይህን ሁሉ የታገሰው ኢየሱስ ጌታ ነው
ሃሌሉያ ሞት ድል ነስቷል
ሃሌሉያ ተነስቷል ጌታ
ሃሌሉያ ክብር እንስጠው
ሃሌሉያ በእልለታ
ሃሌሉያ እልልታ
ሃሌሉያ ሽብሸባ
ሃሌሉያ ሞት ድል ነስቷል
ሃሌሉያ ተነስቷል ጌታ

በሐሰተኛ ምስክር መካሰስን
መገረፍ በጥፊ መመታትን
መጨነቅ በምራቅ መተፋትን
የእሾህ አክሊል መቀዳጀትን
ልብሶች መገፈፍን በበትር መመታትን
ከወንበዴዎች ጋር እንድ ሆኖ መታየትን

በእንጨት መስቀል ላይ መቸንከርን
ሐሞት ኮምጣጤ መጠጣትን/2/
ጎኑ ላይ በጦርም መወጋትን
ነፍስን አሳልፎ መስጠትን

የትንሳኤ

Leave a Comment

Scroll to Top