እግዚያብሔር አምላክ ሆይ ፍጡርን አትዘንጋ
በጨለማ የሚጓዝ የህዝብህን መንጋ
ሰላምን ተጠምቶ እጆቹን ሲያነሳ
ልቡ ተስፋ ቆርጦ ተከቦ በአበሳ
አለም ተሸብሯል በጦርነት መቅሰፍት
ፍቅር ሰላምን ላክ እየሱስ የኛ አባት
አማኑኤል ሆይ ና ግዛትህን ጐብኘው
የጠማውን ሰላም ህዝብህን አጥግበው
እመቤቴ ማርያም የብርሐን መንገድ
ህዝብሽን ሰብስቢ አድርጊያቸው በአንድ
የህይወት ምንጭ ኢየሱስ ሰላም ተጠምተናል
ሁሉንም ትተነው አይንህን ናፍቀናል
ዙሪያችንን አየን በሙሉ ጨልሟል
ፈተናውም በኛ ላይ ድልን ተመኝቷል
የኛ አባት እግዚአብሔር ድልድዩን አሻግረን
ከወንድሞቻችን አንድ ላይ ደባልቀን
ለሐገራችን ኢትዮጵያ ሰላምን ስንለምንህ
ገናናው አባት ሆይ እንዳይርቀን ፍቅርህ
ህዝቧን ፍሬዋንም ባርክልን በክንድህ
ዛሬም ለዘለአለም ክበር እንበልህ
ተሰማህ ወይ ድምፄ ከጨለማው ጉዳጓድ
ቆጠርከኞይ እኔን ከሰጐችህ እንደአንድ
ሰላምህን ለኔ ልታፈስ መጣህ ወይ
ፈቀድክ ሆይ እንዳይህ ሰውነት ጌታዬ ሆይ
