ጌታዬ ጠብቀኝ

24

ቃልኪዳኔን ከአንተ ጋር አፀናለሁ
ዳግም ለአለም ባሪያ ሳልሆን ወስኛለሁ
ከአንተ ጋር ልጓዝ አሁን እጀምራለሁ
እንግዲ ጌታዬ ሕይወቴን አደራ እላለሁ

ካንተ ሌላ ማን እረዳት አለኝ
በጉዞዬ የሚጠብቀኝ
የጠራኸኝ ያፈቀርከኝ
አንተው ጌታ አሁንም ጠብቀኝ

በአንተ የተመካ በፍቅርህ የታሰረ
እንደፍቃድህ የሚኖር በእምነት የጠነከረ
ጠላትን ድል ነሳ ታማኝ ወታዴርህ
እኔንም አስታጥቀኝ እንድኖር ለክብርህ

በትግል ሜዳ ላይ ተሸንፌ እዳልወድቅ
በሐይልህ ደግፈኝ ካንተ እንዳልቀር
ጉዞዬ እረጅም ነው አምናለሁ አባቴ
እንዳልታክት ጌታ ሆይ ሁነኝ እረዳቴ

የትንሳኤ

Leave a Comment

Scroll to Top