እየኝ በምህረት እየኝ እየኝ በፀጋህ እየኝ
መስቀልህ ስር አለሁ ምህረትህን ላክልኝ
አይዞህ ብለህ ዳብሰኝ ድምፅህን ናፈቅኩኝ
አንተን ተጠለልኩኝ
ያደንዳናው ልቤ በፍቅርህ ተሰብሮ
ከእግርህ ስር አኖረኝ እጅና እግሬን አስሮ
ምህረትህን ላክልኝ ነፍሴ ትሻሃለች
በደምህ እንድታጥባት መስቀልህ ስር አለች
ከፊትህ ቆማለች
ድርሻዬን ወስጄ ከቤትህ ስወጣ
መስሎኝ ነበር እኔስ እማያየኝ ጣጣ
ብጣር መብላት አምሮኝ ኣሳሬን እያየሁ
እባክህ ይቅር በለኝ ይኸው እጅ ነሳሁኝ
ፊትህ ተደፋሁኝ
ማን ኣለብኝ ብዬ ዘራፍ ስል ሳጓራ
ነፍሴ ተጠባለች በሀጥያት ተዋቅራ
በቃኝ ለዘላለም ልመንህ ያንተ ልሁን
እባክህ ከመስቀል ዘንበል ብለህ እየኝ
በመንግስትህ አስበኝ
