ልታመንህ እንጂ

32

ልታመንህ እንጂ በአንተ ልደገፍ

ጭንቄን ሁሉ ልርሳ እስኪ ልረፍ
አንተ እያለህልኝ እረዳቴ
ስጋት አይገባኝ በህይወቴ

ሸክሜን ሁሉ በአንተ ላይ ጥዬ
እርፍ ልበል ተደላድዬ
ለምን ልጭነቅ ለምንስ ልስጋ
አንተ እያለህ ከእኔ ጋራ

አንተ ባትረዳኝ ባትሆነኝ አቅም
ያለፍኩት ዘመን አይታለፍም
ዛሬም በአንተ ላይ ልቤ ይታመናል
ሁኔታን አይቶ መቼ ይሰጋል

መታመኛዬ በእድሜ ዘመኔ
ለእኔ ኣንተ ነህ ኢየሱስ መድህኔ
አፅንቼዋለሁ ልቤን በአንተ ላይ
አብልጬሃለው ከምንም በላይ

መኖርስ በአንተ ክንድህን ተማምኖ
ከእምነት ፅናት ካንተ ጋር ሆኖ
ታስመካለህ በአንተ እንዲኮራ
አይነዋወጥም በጠላር ሴራ

የትንሳኤ

Leave a Comment

Scroll to Top