ሰላምህን ስጠን /2/

33

የሱስ ሰላምህን ስጠን
የአንተን ሰላምህን ስጠን

ኢየሱሴ ፍቅርህን ስጠን
አኑረን በሰላም ያዘን

እሰጣለሁ ብለህ ቃል እንደገባኸው
ለሐዋሪያቶች እንደተናገርከው
ዛሬ እንሻዋለን ዛሬ ያንን ሰላም
እባክህ ስጠን እርሱ ነው የሚረባን

ዘላቂ የሚሆን እስከ መጨረሻ
በዕድቅ የሚያቆመን ይህን አለም መርሻ
ሰላምህ ነው ስጠን ስንኖር በቤትህ
አምረን እንድንታይ ሆነን በአንድነትህ
ቆመን በህብረትህ

ፍቅር እንደገባን ከአንተ እንደተማርን
በስምህ ለመኖር እንደተዋደድን
በመንፈስህ ተገኝ በመካከላችን
የሰላም መሳሪያ ይታይ መሆናችን

የትንሳኤ

Leave a Comment

Scroll to Top