የሚረዳኝ የሚያግዘኝ

33

የሚረዳኝ የሚያግዘኝ የለምና ከእኔ አትራቅ
የደስታዬ የሰላሜ ምንጭ እኮ ነህ ያዝ እጄን አትልቀቅ

ብቸኝነት ህይወቴን ሲከባት
ሲያናውጣት እጅግ ሲፈትናት
አቅሜ አልችልም ይከብደኛል ለኔ
ቶሎ ናልኝ ቶሎ ና መድህኔ

ደስ አይለኝም አንተ የሌለህበት
በመንፈስህ ያልተገኘህበት
ከጐኔ ሁንልኝ ረዥም ነው የኔ መንገድ
ካንተ ሌላ እኔ የለኝም ዘመድ

እኔ አልሻም እኔን የሚረዳ
የተነሳ ከደምና ስጋ
አንተ ሁነኝ ምርኩዜ እረዳቴ
ኢየሱሴ ይሄ ነው መሻቴ

የትንሳኤ

Leave a Comment

Scroll to Top