ተመለሽ ሃገሬ ኢትዮጵያ ፊትሽን አዙሪ
ከማንም ከምንም በላ እግዜርን ፍሪ
ተመለሽ ሃገሬ ኢትዮጵያ ፊትሽን አዙሪ
ከማንም ከምንም በላይ እግዜርን ስሚ
ጥበብ መጀመሪያ እግዜርን መፍራት ነው
ወንዱ ሴቱ ወጣቱ አዛውንቱ ይንበርከክ በፊቱ
ምሕረቱ ለዘላለም ነውና /4/
እስኪ አስተውይው ዛሬ ያለሽበትን
ችግር ጉስቁልና በዙሪያሽ ያለውን
ከዚህ ሊታደግሽ ጌታ በደጅ ነው
በፊቱ ውደቂ ዛሬም ምሕረቱ አለው
ሃያላን ነገሥታት ጠቢባን ቢሆኑ
ስላንቺ መፍትሔ ማምጣትን አልቻሉ
መሮጥ መቅበዝበዝ ዛሬስ ይበቃሻል
ተመላሽ ኢትዮጵያ ጌታ ይሻልሻል
የተስፋ ቃል ያለሽ ኢትዮጵያ አድምጪ
የልብሽን ጆሮ ለእግዜር ስጪ
ምትጎበኝበት ዘመኑ ቅርብ ነው
ቃሉን የሚረሳ ጌታ ሰው አይደለም
