ፍቅር ያሻዋል

38

መከራና ስቃይ ተፈራርቀውበት
ረሃብና እርዛት መጠማት በዝቶበት
ፍጥረት በኃጢያቱ መውደቁ ሲያንሰው
ጌታ ሆይ ሀዘኑን ከእርሱ ወዲያ አርቀው
የክብርህን መገለጥ የመምጣትህን ዜና

ለእርሱ ግለፅለት ቶሎ ቅረብና

ፍቅር ያሻዋል ያስፈልገዋል
ፍቅር ያሻዋል ይታደገዋል

በአምሳልህ የሰራኸው እስትንፋስን ሰጥተህ
የተጠበብክበት በእጅህ አበጃጅተህ
ፍጥረትህን እንዲገዛ ስልጣን የሰጠኸው
የምድርን ፍጥረታት በእጁ ስር ያረከው
ያ ልጅህ ያንተ ክብርህን የሚጠብቀው
ተቅበዝብዟል ጌታ ከታችህ ነው ያለው

ልታኖረው ወደህ መልካምን አስበህ
አንተ ወደመረጥከው ልትመራው ፈቅደህ
ግን ሳያውቅ ቀረና የት እንዳለህ አንተ
አጠገቡ ሳለህ ያው ተንከራተተ
እጁን ይዘህ ምራው ወዳለህበት
አይኑን ዳስህ አብራው እንዲያይበት

የትንሳኤ

Leave a Comment

Scroll to Top