ልቤን ኑርበት

39

በእኔ እየኖርክ ያንተ ስላረከኝ

መላ እኔነቴን ጌታ ብሰጥህስ
ዛሬ ታዲያ እኔ ቆሜ ብዘምር
ውዴ ካረከው ጋር አይወዳደር /2/

ኑሮን ባንተ እኖራለሁ
አንተም በእኔ ትኖራለህ
እረኛዬ ጠባቂዬ
አትለየኝ መኖሪያዬ

ሁሉ ሲተወኝ አንተ አልተውከኝ
እንድጠፋ ችላ አላልከኝ
ብቻህን ነው የረዳኸኝ
ቃልን ሰጥተህ ያፅናናኸኝ

ማዕበሉን ወጀቡን ያሳለፍኩብህ
ደስታዬን ሰላሜን ያገኘሁብህ
እጄን ጠበቅ አርድርገኝ ለቅቄህ አልቆምም
ካንተ ተለይቼ ህይወት አላየሁም /2/

አንድ መላ ማውቀው አንተን መያዜን ነው
ትልቁ ጥበሴ አንተን መቅረቤ ነው
እንጂማ በራሴ ስጋዬ ደካማ
አቀናኸው እንጂ መድረሻዬንማ /2/

ካንተ በሆነልኝ የመንፈስ እረፍት
ደስታዬ እንዲያፀናው ዳግም በመንግስትህ
ከስጋ ማሰሪያ ሃይልህ ነፃ ያውጣኝ
ልቤን ንገስበት ሌላ ሌላ እንዳላይ /2/

ልቤን ኑርበት ማንም አይጋራህ
እንጂ እራሴን ሰጠሁህ

የትንሳኤ

Leave a Comment

Scroll to Top