ቀና /2/

40

በል አለኝ ቀና /2/
ልበል ቀና ቁዘማን ልተውና
ልበል ቀና ሀዘኔን ልርሳውና
ልበል ቀና ሸክሜን ልስጠውና
ልበል ቀና በኢየሱስ ቀና አለና

ዓይኖቼን ቁልቁል ከፍቼ ሳብሰለስል ቆይቼ
ስለምን ይመሽብኛል አንገቴን እንዲሁ ደፍቼ
እግዚአብሔር ሲያቀናኝ ቀናሁ ሲመጣ ጭንቀቴም ቀረ
ብዙ ቀን ከፊቴ አሊ ደግሞ ለእኔ የተፈጠረ

ፍፁም አላየሁም በዘመኔ እኔ
ፃድቅ ተረስቶ ተጥሎ በዓይኔ
ቀና ይላል እንጂ ጊዜው መጥቶ /2/
በእግዚአብሔር እረክቶ
በነፃነቱ ልኖር ክርስቶስ ነፃ አወጣኝ

ውብ አለምን በፊቴ አኖረው እንዲደላኝ
በሰበብ በምክንያቱ መቆዘም መጠበቤ
መጠራቴ አይደለም ኧረ ቀና በል ልቤ

አልቆምም ድምፁን ሰምቼ ጠላቴን በዚህ ሰግቼ
ዕንቅብን አልደፋበትም መክሊቴን በእጄ ላይ ትቼ
ሲመስለው ይኖራል እንጂ ዝማሬ ከእኔ እንደቀረ
እ/ር ያዘምረኛል እንዲህ እያከበረ

ጅማሬ ነው ይሄ ቀን መጣ ቀና…..
አምላክ ይስጠኝ እንጂ ዕድሜና ጤና…..
እዘምራለሁኝ ገና /3/

ገና /2/ ዜማ አለኝ ገና
ገና /2/ ገና ነኝ ገና
ገና /2/ መቼ ጀመርኩኝና
ገና /2/ጭብጨባም አለኝ ገና
ገና /2/ መቼ ዘመርኩኝና
ገና /2/ እዘምራለሁ ገና
ገና /2/ ሽብሸባም አለኝ ገና
ገና /2/ የምለው አለኝ ገና
ገና /2/ ቆይቼም አለኝ ገና
ገና /2/ ለነገም አለኝ ገና
ገና /2/ ዝማሬም አለኝ
ገና /2/ ግጥምም አለኝ ገና
ገና /2/ ቅላፄም አለኝ ገና
ገና /2/ እልልታም አለኝ ገና

የትንሳኤ

Leave a Comment

Scroll to Top