ፀሎቴ

41

እገዛህ …እገዛህ ሁሌ አይለየኝ
ኦ…ጌታ ሆይ በፀጋህ ደግፈኝ / ደግፈኝ

እገዛህ ሁሌ አይለየኝ
በፀጋህ አቅፈህ ደግፈኝ
በሀሳብህ ሁሌም አስበኝ
ያላንተ የሱስ ማንም የለኝ

ከዚህም በላይ ላክብረው
መንፈስህን ከእኔ አትውሰደው
ኃይልና ብርታቴ ሆነህ
በስጦታዬ ታይ ገነህ
ታይ ገነህ ታይ /3/

ከትላንትናው ተሽዬ ዛሬ
እንድሮጥልህ እንዳይዝል እግሬ

ምራኝ ጌታዬ ወጥተህ ከፊቴ
አቅም አልጣ በኣገልግሎቴ…ነው ፀሎቴ

ኑሮዬ እንዲኖር ድል ያለው ህይወት
ያስፈልገኛል ያንተ መገኘት
ድጋፍህ ይኑር በጥረቴ ላይ
የምትወደው የልብህ አገልጋይ…
ሆኜ እንድታይ

እንዳልወሰድ በዓለም ፈተና
ሞልቶ እንዳልረሳህ በብልፅግና
ቃልህ በልቤ ዘወትር ይንደድ
ወደአንተ ልምጣ በዳዊት መንገድ…
ይህን ልውደድ

የትንሳኤ

Leave a Comment

Scroll to Top