ደመና ይውረድ ይወረድ
የክብር ደመና ይወረድ ይወረድ
የፍቅር እሳት ይንደድ ይንደድ/2/
1. እኔ ተኝቻለሁ መንፈሴ ግን ነቅቷል
ይህ የውዴ ቃል ነው በራፉን ይመታል
ነፍሴ ሆይ ተነሺ ውዴን አስተናግጂው
ሰፍረህ የማትሰጠው በይና ጠይቂው
ውዴ ሆይ
ደመና ይውረድ ይወረድ
የክብር ደመና ይወረድ ይወረድ
የፍቅር እሳት ይንደድ ይንደድ
2. እጁን በቀዳዳ ደግሞ ሰደደና
የተኛሁበትን አንኳኳ እንደገና
አንጀቴም ስለርሱ እጅግ ታወከና
ለውዴ ከፈትኩኝ ሞላኝ በምስጋና
ውዴ ሆይ
ደመና ይውረድ ይወረድ
የክብር ደመና ይወረድ ይወረድ
የፍቅር እሳት ይንደድ ይንደድ
3. በእኔ ላይ ያለው አላማው ፍቅር ነው
ውዴ ሆይ በፍቅርህ ተነድፌአለሁ
ካልባረከኝ የሱስ አለቅም ብዬአለሁ
መጉናፀፊያዬን እኔው እጠብቃለሁ
ውዴ ሆይ
ደመና ይውረድ ይወረድ
የክብር ደመና ይወረድ ይወረድ
የፍቅር እሳት ይንደድ ይንደድ
4. ተራራውን ውዴ አልፈህ ትመጣለህ
ጌታ ሆይ ስጠራህ ከተፍ ትላለህ
የጠላቴንም ቀንድ ከእግሬ ትጥላለህ
ፍቅርህን ለአህዛብ በሐይል ትገልጣለህ
ውዴ ሆይ
ደመና ይውረድ ይወረድ
የክብር ደመና ይወረድ ይወረድ
የፍቅር እሳት ይንደድ ይንደድ
