በመንፈስ ቅዱስ እንመን

43

አህዛብ ሁላችን በመንፈስ እንኑር
ምድራዊ ስራችን በፅኑእንመርምር
በመንፈስ ቅዱስ ሐይል እንድንጠነክር
የእግዚአብሔርን ማዳን ዘወትር እናብስር

ቅዱሳን ሰማእታት በክብር አልፈዋል
በፀጋ ተሞልተው በመልካም ፈፅመዋል
እኛም እንበርታ ጉዞአቸውን እንከተል
በዚህ አለም ብልጭልጭ ከቶ እንዳንታለል

የጰራቅሊጦስ መልእክት ለሁላችን ይድረስ
በጌታ መንፈስ ሐይል ነፍሳችን ትታደስ
በጐ አላማችን ከግብ እንድናደርስ
ከክፉ ኑሮኣችን በቶሎ እንመለስ

በእግዚያብሔር መንፈስ እንታመን

በሕይወት ጉዞአችን እንዲከተለን
በድንቅ ተአምራቱ እንድንድን
በመንፈስ ቅዱስ እንመን

የትንሳኤ

Leave a Comment

Scroll to Top