ኦ ፈጣሪ መንፈስ ናልን
የመንጐችን ነፍስ ጐብኝ
የላይ ፀጋህንም ላክልን
አንተ ነህ ፈጣሪያችን
አማካሪ ጥበብ ነህና
ያምላክ ፀጋው ልኡል ነህና
የሕያው ፍቅር ምንጩ ነህና
እውነተኛ ብርሐን ነህና
የሰባቱ ሐብቶች ጸጋ ነህና
የአብ ቀኝ ስልጣን ነህና
ትንቢቶች ቀድሞ የተናነሩት
ፍፃሜን ዛሬ አገኙ
ለነፍሳችን ብርሐን ሁንልን
የአንተን ፍቅር ሙላብን
በድካማችን ሁሉ አበርታን
የዘለአለምን ንቃት ስጠን
የነፍሳችንን ጠላት አርቅ
ሳይቆይ ሰላምን አምጣልን
ምክርህንም እንድንወድ
ከክፉም እንድንወገድ
አብን እንድናውቅ አብቃን
አንድ ልጅህንም አስረዳን
በአንድነት በመንፈሳቸው ነህና
እምነታችን በአንተ ነውና
ለአብ ክብር ስብአትም
ለልጁ በትንሳኤውም
ለመንፈስ ቅዱስ ለአማካሪውም
ለዘለአለም ይሁን ምስጋና
አሜን ::
