መንፈስ ቅድስ ሆይ ናና ናና
ነፍሴ በደስታ ትቀበልሃለችና /2/
1. ፍሬው ያማረ እንዲሆን ስራችን
የአንተው አድርገው ተግባራችንን
እውነተኛ ሰላም እባክህ ስጠን ጌታችን
የሰማዩ አምላክ አንተ ብቻ አባታችን
መንፈስ ቅድስ ሆይ ናና ናና
ነፍሴ በደስታ ትቀበልሃለችና /2/
2. የእውነተኛ አምላክ ወደኛ መጥተህ
ልባችንን አፅንተን ልንቀበልህ
ተስፋ ያጣች ነፍስ ምራት ድረስላት ፈጥነህ
መውደቂያ የሌላት ሆና እንዳትቀር በፊትህ
መንፈስ ቅድስ ሆይ ናና ናና
ነፍሴ በደስታ ትቀበልሃለችና /2/
3. ኦ መንፈስ ቅዱስ አንተ ብቻ ሁን ብርሃናችን
በማያልቀው ፀጋህ ዘወትር ጠብቀን
በቅን በመልካሙ በህይወት መንገድህ ምራን
ወራሾች ሆነን በሰማይ መንግስትህ አድርስን
መንፈስ ቅድስ ሆይ ናና ናና
ነፍሴ በደስታ ትቀበልሃለችና /2/
4. ፍፁም በአንተ አምነን ልንገኝ ፀጋህ አይለየን
ዘወትር በመንፈስህ እንድመራ አድርገን
ሁሉን ቻይ ኤልሻዳይ እውነተኛ አምላክ መጥተህ
እነሆ በፊትህ ቆመናል ጌታ አፍስስ መንፈስህን
መንፈስ ቅድስ ሆይ ናና ናና
ነፍሴ በደስታ ትቀበልሃለችና /2/
