ኦ መንፈስ ቅዱስ መጣን ልንለምንህ
ምኞታችንን ፈፅምልን
ና አርቅልን ጨለማውን
ፍቅርህን ስጠን
ኦ ዘለአለም ብርሃን
ፍፁም ደግነት አንተ ነህና
የጥበብ መንገድ ምንጩ ነህና
ከሰይጣን ሞገድ ነፍሳችንን አድናት
አውጣን ከእንቅፋት እውቀት
ኦ የዘለአለም
ነፍሳችንን በፅድቅ ምራት
አትምብን የእግዚአብሔርን ፍርሐት
ዘወትር ቀስቅሰን ስጠን ንቃት
ሁነን ብርታት
ኦ ዘለአለም ውበት
ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ
እናዚም ከልብ እንወድስህ
ይሁን ክብር ስግደት ስብአት
ለዚህ ትልቅ ሚስጥር
ኦ ዘለአለም ፍቅር
