አለልን መንፈስ ቅዱስ

45

በአዲሱ መሳሪያ ቀርቶልን ሰበሬ
አርሰን እንድናፈራ የመንፈስን ፍሬ
አምራች እንድንሆን ጠንካራ ገበሬ
ፍቅር ደስታ ሰላም እንድናገኝ ዛሬ

ለክፉ ክፉ ሳይሆን ፍፁም መታገስ
ትቢትን አርቀን እንድንችል መጥበስ
እጃችን እንዳያጥር ላሰው ከመለገስ
ይህን ሁሉ ስራ ከመስራት የሚያደርስ

እራሳችንን ጋስተን ፀንተን እንድንዘልቅ
እንደ ህፃን ሆነን ምንም እንደማያቅ
ታማኝ ሆነን እንድንኖር በሐጥያት እንዳልወድቅ
የሳት ቅጥር ሆኖ ከሰይጣን የሚጠብቅ

ድንቅ ታመራትን ላመስራት የሚችል
ከህመም ከስቃይ ከችግር የሚያስጥል
በጠየቅነው ሰአት ወዲያው ከተፍ የሚል
በፈተና ግዜ የሚያቀናጀን ድል

የትንሳኤ

Leave a Comment

Scroll to Top