አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ

47

አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ
የሰማይ የምድር ፈጣሪ ንጉስ
ሶስት አካል አንድ አምላካችን
አንተ ነህ ፈጣሪያችን

ለአሰራርህ ወደር የሌለህ
አንተ ብቻህን እግዚአብሔር ነህ
አትሳሳትም ሁሉን ታውቃለህ
ከሁሉ በላይ ታላቅ አምላክ ነህ

ሁሉን ስትፈጥር ማን አግዞሐል
አንተ ብቻህን መንግስት ሰርተሀል
የእጅ ስራህም ይመሰክራል
ውብ አምላክ ነህ ማን ይመስልሐል

ታላቅ አምላክ ነህ ኣመልክሐለው
ቅዱስ ንጉስ ነህ እስግድልሐለው
ሌት ተቀን ስምህን አሞግስሐለው
የህይወቴ ንጉስ አነግስሐለው

ነውር የሌለህ እውነተኛ አምላክ
በሰማይ በምድር የምትመለክ
አንተ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ነህ
ዘለአለማዊ ጊዜ የማይሽርህ

የትንሳኤ

Leave a Comment

Scroll to Top