ገና ብዙ መንገድ እፊቴ እያለ
ገና ሳልጀምረው ጉልበቴ ዛለ
መከሩ እጅግ ብዙ ሆኖ ሣለ
ለመከሩ ስራ ልቤ ዋለለ
ስለዚህ ጌታ ሆይ በመንገድ እንዳልቀር
በፈተና ብዛት በብዙ ችግር
ደካማነቴን ከኔ አርቅልኝ
ፀጋህን አብዛልኝ ሁሉን አስችለኝ
አስችለኝ አስችለኝ አስችለኝ
አስችለኝ አስችለኝ አስችለኝ
መንገዳ አስቸጋሪ በሯም ጠባብ ናት
አሜኬላ እሾህ እጅግ የበዛበት
እሻሁ እየወጋ እግሬን አደማኝ
ልቤም ተሸነፈ እጅግ መረረኝ
ስለዚህ ጌታ ሆይ ጫማን አድርግልኝ
አሜኬላ እሾሁ እንዳያቆስለኝ
የፀጋህን ልብስ ቁርበትን አልብሰኝ
ሁሉን በሚያስችለው ሁሉን አስችለኝ
ወንድሜ ሲበድለኝ ይቅር ማለት
አልቻለም ልቤ ቂም አሸንፎት
አሳዳጆቼን በመመረቅ ፈንታ
ለበቀል ተነሳሁ አልቻልኩም ጌታ
የበደለኝን ይቅር ብዬ እንዳልፈው
ቂመኛ ልቤን ጌታ ሆይ ለውጠው
ሁሉን እችላለሁ ሐይልን በሚሰጠኝ
እንደተባለው እኔንም አስችለኝ
