ልረስርስ /3/
በአንተ ልረስርስ /2/
መንፈስ ቅዱስ ጌታዬ አንተ ሁነኝ ከልቤ
ልብህም ይራራልኝ እየኝ ስታየኝ ተርቤ
የሕይወቴ ምሶሶ መንፈስ ቅዱስ አንተ ነህ
ደንዳናውን ስበረው ደረቁን አረስርሰው
መናገርም ይቅርብኝ ዝም ልበል አርፌ
ብለፈልፍ በስጋ ፀፀት ጭንቀት ነው ትርፌ
በአይምሮዬ ባሰላ ሕይወትን አልደርስባት
ያላንተ ሆኖብኛል ሰማይን በእጅ መንካት
መንፈስ ቅዱስ ጌታዬ አንተ የኔ መከታ
ትጥቄ ጦሬ ከሆንከኝ ማነው እኔን የሚረታ
መባከኔን ሰብስበህ መድከሜን ሃይሌ ሆነህ
አረስርሰኝ ልጅህ ጉልበቴን አበርትተህ
የደረቁ አጥንቶቼን እስትንፋስን ስጣቸው
ሥጋና ደም ጅማትን ጌታ ኣንተ ሙላቸው
በሸለቆ ያሉትን ሙቶች ሕይወት ስጣቸው
አረስርስው ይለምልሙ ጸንተው ይቁም ቤታቸው
ከባርነት አውጣኝ ነፃነቴን መልስ
በጣም እፈልጋለሁ ተፈቶ አንተን መወደስ
መሻቴ አንተ ነህና ናፍቆቴ አንተ ነህና
የደረቀውን አረስርስ መንፈስ ቅዱስ ሆይ ና
