ቅዱስ ስሉስ ሆይ የኛ ዋስ ጠበቃ
በአምሳልህ ፈጠርከን ለክብርህ እድንበቃ
አለምን አስውበህ ፈጥረህ የሰጠኸን
አብ ወልድን መንፈስ ቅዱስ ኣንተ ነህ ጌታችን
ሚስጥርህ እረቂቅ ነው በሰው የማይደረስ
ስራህም ድንቅ ነው የልብን የሚያደርስ /2/
ጨለማና ብርሃን መፈራረቃቸው
የአንተ የስላሴ ድንቅ ስራ ናቸው/2/
አብ አባት ሆነኸን ልጅህን ላክልን
ወልድም ደግሞ ሞተህ አዳንከን ከሲኦል/2/
መንፈስ ቅዱስ ጌታም አፅናናኸን እኛን
እናድስ ምስጋና ቅዱስ ስሉስ እያልን/2/
ሶስት አካል አንድ አምላክ ቅዱስ ስላሴ ሆይ
ጠብቀን መሪያች ከአንተ እንዳንለይ/2/
በላይ በሰማያት ከዙፋን ስር ሆነን
እንድናመሰግንህ ቅዱስ ስሉስ/2/
