ነፍሴ በደስታ

64

ነፍሴ በደስታ
ላረገላት /ለዋለላት/ ጌታ
እጆቿን ዘርግታ
ትዘምር በእልልታ
ትዘምር በእልልታ /2/
ታመስግን በእልልታ የረዳትን ጌታ

ያክፉ ዘመኗን ፍፁም እረስታለች
የሀዘን ማቋን ጥላ ኢየሱስን ለብሳለች
ታገልግለው ከልብ ይህን ታላቅ ጌታ
በቅዱስ ጉባኤ በሐሴት ተሞልታ

ድንቅ ተአምር አይቶ ስንቱ ሰው ሲናገር
ስለ እግዚአብሔር ክብር ቆሞ ሲመሰክር
እኔም አለች ነፍሴ ከሰፊ እጁ በልታ
ተመስገን ትላለች አትሻም ዝምታ

ግራቀኝ ጠፍቶ እርቋት መድረሻ
ኢየሱስ ነው የሆናት ለነፍሴ መሸሻ
ወደ ኋላ የለም የሚቀር ከሱማ
የሆታ የእልልታ ድምፆቿን ታሰማ

የትንሳኤ

Leave a Comment

Scroll to Top