የምህረት አምላክ

65

የምህረት አምላክ የምህረት ንጉስ
ሀሌሉያ ክበር እየሱስ
የምህረት ጌታ ምህረት የሞላህ

ዘወትር ከፍ በል የአለሙ መሲህ

ሐጥያት በሞላበት በአንዲት አገር
ፃድቃን ቢኖሩ ያነሱ ከቁጥር
ስለፃድቆች ሲል ጌታ ይምራል
ሰፊ ምህረቱን ከላይ ያዘንባል
የሰራዊት ጌታ የናብርሐም አባት
ይቅር ባይ አምላክ ሞልቷል ምህረት

እንደ ምህረቱ እንደ ፍቅሩ ሳይሆን
በክፉ ስራ በአመፃችን
ጎመራና ሰዶም እንደወደሙት
እኛም ያለነው አሁን በሕይወት
በሞትን ነበር ጭራሽ በጠፋን
በዚች ምድር አስካሁን ላይቆምን

በእላይ በአርያም በምህረት ዙፋን
ተቀምጦ ጌታ ያ ፈጣሪያችን
የማያልቀው ምህረቱን ለሁሉም ሰጥቶ
በልጁ ደም እኛን አንፅቶ
ሐጥያታችንን በጀርባው ጣለ
ሙሉ ምህረትን ለኛ አደለ

የትንሳኤ

Leave a Comment

Scroll to Top