አቤቱ ከአሕዛብ መካከል እናመስግንህ
በወገንም መካከል ለአንተ እንዘምርልህ
ምህረትህ በሰማይ ትልቅ ናትና
እውነትህም እስከጥልቅ ድረሰ ነውና
በድካማችን ጊዜ እረድኤት የሰጠን
በአምላካችን ሁሌ ድል እናደርጋለን /2/
የሐያላን ሐያል ቃሉ የሚፈውስ
ከፀሐይ መውጫ እስከ መግቢያው ድረስ
ሳሩ ይጠወልጋል አበባውም ይረግፋል
የጌታ ቃል ግን ለዘለአለም ይኖራል /2/
ክፋት ግብዝነት ቅናት ትተን
ተንኮልንም ፍፁም ከልብ አውጥተን
ነፍስን ከሚወጋ ምኞት ሁሉ እርቀን
አምላክን እናክብር ከአሕዛብ መካከል ሆነን /2/
