ሶሰት ሳለችሁ

66

1. የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር
ለዘለአለም ሁልጊዜ የምትኖር
ያን አንዱን ልጅህ ስለምትወደን
ለኛ ለሰዎች አንተ ሰጠኸን

የኛ እግዚአብሔር በሁሉ ቦታ ይድረስህ ክብር
መድሐኒያለም ስምህ ይመስገን እስከ ዘለአለም
መንፈስ ቅዱስ አፅናኝ ነህና ስምህን እናወደስ
ከልባችን እንዘምራለን እያልን ተመስገን

2. ጌታ ኢየሱስ መድሐኒታችን
ከራስህ አብልጠህ እኛን ወደድከን
በሞታችን አንተ ሞትክልን
የዘለአለም ሕይወት ሰጠኸን

የኛ እግዚአብሔር በሁሉ ቦታ ይድረስህ ክብር
መድሐኒያለም ስምህ ይመስገን እስከ ዘለአለም
መንፈስ ቅዱስ አፅናኝ ነህና ስምህን እናወደስ
ከልባችን እንዘምራለን እያልን ተመስገን

3. መፅናናት ምትሰጥ በችግራችን
አይዞአችሁ የምትል ሐዘን ላይ ሳለን
ሰዎችን ወደ እውነት የምትመልስ
አንተ ነህ ጌታ መንፈስ ቅዱስ

የኛ እግዚአብሔር በሁሉ ቦታ ይድረስህ ክብር
መድሐኒያለም ስምህ ይመስገን እስከ ዘለአለም
መንፈስ ቅዱስ አፅናኝ ነህና ስምህን እናወደስ
ከልባችን እንዘምራለን እያልን ተመስገን

4. እግዚአብሔር አብ ልጁ ኢየሱስ
እንዲሁም አፅናኝ መንፈስ ቅዱስ
ሶስት ሳላችሁ አንድ የሆናችሁ
በአለም ሁሉ ይክበር ስማችሁ

የኛ እግዚአብሔር በሁሉ ቦታ ይድረስህ ክብር
መድሐኒያለም ስምህ ይመስገን እስከ ዘለአለም
መንፈስ ቅዱስ አፅናኝ ነህና ስምህን እናወደስ
ከልባችን እንዘምራለን እያልን ተመስገን

የትንሳኤ

Leave a Comment

Scroll to Top