ስንደክም ስንዝል ሀይሉ ይገለጣል
ፀጋውን እያበዛ ብርቱ ያደርገናል
ዲያቢሎስ ሲዋጋን ወድቀን እንዳንቆስል
ሁሌ ይጠብቀናል ጋሻ ሆኖልናል /2/
መልካሙን ከክፋ መለየት እንድንችል
መንፈስህን ልከህ ሰጠኸን ማስተዋል
በቃልህ እየመከርክ ከጥፋት መለስከን
ድንቅ መካሪ መሆንህን በአይናችን አየን /2/
ሐጥያታችንን በደምህ አንፅተህ
በመገረፍህ ቁስላችንን ፈውስህ
ነፃ አወጣኸን በመስቀል ተሰቅለህ
ፈዋሻችን ጌታ ይክበርልን ስምህ/2/
ሐያልነትህን ታማኝነትህን
ታላቅነትህን ሁሉ ቻይነትህን
ተረድተናልና ጌታ ማንነትህን
ድንቅ ነህ መካሪ ነህ
ፈዋሽ ነህ እንላለን
ድንቅ መካሪ ነህ ኢየሱስ
ፈዋሽ ነህ /2/
ኢየሱስ ጌታ ነህ
