በአፌ መመስከሬ

72

በአፌ መመስከሬ ያንስሐል ኢየሱስ
ቆሜ መናገሬ መቼስ ሊበቃህስ
በእኔ እደርና ስምህን ላሞግስ
ስለክብርህ ልኑር ዘወተር በመቅደስ

ተመስገን ልበልህ ድምፄን ከፍ አድርጌ
ላዚምልህ ለአንተ ፊትህ ተንበርክኬ
ማን አለኝ ማን አለኝ ከቶ እንደ ኢየሱስ
ዘለአለማዊ አባት ሐያልና ቅዱስ

ዝቅ በል እረኛዬ ዓይኔን በአይንህ እየው
የሚፈስ እንባዬ ፊቴን አረጠበው
እጆችህን ዘርጋ አብሰኝ አባቴ
አላሳዝንህም ዳግም በሐጥያቴ

ሐያል ነህ ብርቱ ነህ ምንም ኣይሳንህ
ከቁጣህ አድነኝ ዘውትር በምረተህ
ልዑል ሆይ መንገዴን ጥርጊያውን አቅናልኝ
ያላንተ አልኖርም በቂ አቅም የለኝ

የትንሳኤ

Leave a Comment

Scroll to Top