በሄድኩበት ቦታ ጠባቂ እረኛ አለኝ
በለመለመው መስክ ሁሌ የሚመራኝ
በሞት ጥላ ባልፍም ፈፅሞ አይተወኝም
የጠላት ፍላፃ ፊቴን አይነካውም
እኔስ ከተማመንኩ በኢየሱስ በጌታ
የሚያስፈራኝ የለም በቀን ቢሆን ማታ/2/
በጌታ ታምኜ ከተመላለስኩኝ
ዓለም አይረባኝም ኢየሱስ ከያዝኩኝ
ወጥቼ እስክገባ የሚጠብቀኝ
ከሰይጣን ፈተና ከውድቀት አነሳኝ
የሲድራቅ የሚሳቅ የአብድናጐን አባት
ከእቶን እረመጥ ውስጥ ካዳነኝ ከእሳት
ዛሬም አይሳነውም ይህንን ለማድረግ
ከዚህ ዓለም መከራ እጅን ከመታደግ
